ሥላሴያውያን መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር Trinitarian Bible Society
የTrinitarian Bible Society ሥላሴያውያን መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር በእንግሊዝ አገር የተመሰረተው በ1831 ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበሩ ትክክለኛና ታማኝ የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስ በመላው ዓለም ለሚኖሩ ሕዝቦች ለማስተላለፍ የቆመ የፕሮቴታንት አማኞች ድርጅት ነው፡፡ ስለዚህም በብዙ የተለያዩ ቋንቋዎች የትርጉምን ሥራዎች አሁንም እያካሄደ፣ በሽያጭ ክፋሎቹና በስጦታ መርሃ ግብሮቹ
አማካኝነት መጽሐፍ ቅዱስን እያሰራጨ ይገኛል፡፡
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ፕሮጀክት
አማርኛ ቋንቋ ከ22 ሚሊየን በላይ በሆኑ ሕዝቦች የአፍ መፍቻ ቋንቋ ሲሆን በዓለም ውስጥ በስፋት ከሚነገሩት የሴሜቲክ ቋንቋዎች መካከል አንዱና የራሱ መጻፊያ የጽሑፍ ፊደላት ያሉት ነው፡፡ ከሴሜቲክ ቋንቋዎችም መካከል በተናጋሪዎች ብዛት ከአረብኛ ቀጥሎ ሁለተኛው ቋንቋ ነው፡፡
የ Trinitarian Bible Society ሥላሴያውያን መጽሐፍ ቅዱስ
ማህበር፣ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ አማርኛ
ቋንቋ የመተርጎም ሥራን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ይህ አዲስ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ
ትርጉም የሚከናወነው ከታመኑ የመጽሐፍ ቅዱስ
ትርጉም ምንጮች
ላይ ነው፡፡ ስለሆነም አዲስ ኪዳኑን
ከግሪኩ Received Text of the New Testament ወይንም ከ ቅቡሉ የአዲስ ኪዳን
ቅዱስ የግሪክ መጽሐፍ ሲሆን፣ የብሉይ
ኪዳኑ
ትርጉም ደግሞ ከሒብሩው ቋንቋ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ The Masoretic Hebrew Text
ማሶሬቲክ የብሉይ ኪዳን ቅዱስ
መጽሐፍ
ላይ ነው፡፡
ከነዚህ ታማኝ የእግዚአብሔር ቃል የትርጉም ምንጮች ባሻገር ተርጓሚው የመጽሐፍ ቅዱስ ልዩ ልዩ ሶፍት ዌሮችን፣ መዝገበ ቃላቶችን እና ኢንተርሊኒየሮች (የመጀመሪያው ቋንቋ በጽሑፉ የላይኛው መስመር የእንግሊዝኛው ቀጥታ ትርጉም በታችኛው መስመር ላይ በተዘጋጁ ቃል በቃል ትርጉሞች) እንዲሁም ሌሎች መርጃዎችን በመጠቀም በዘመናዊ የአማርኛ ቋንቋ በጣም ጥሩ የሆነ ትርጉምን ለማዘጋጀት በእግዚአብሔር እርዳታ
ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ትርጉሙ Trinitatian Bible Society በሥላሴያውያን የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር የበላይ ተቆጣጣሪነት የሚመራ ሲሆን፣ ትርጉሙ ተጠናቆና ታትሞ ለአንባቢዎች ሲቀርብ ለጥንታዊ የእግዚአብሔር ቃል ምንጮች በጣም ታማኝ የሆነና ለኢትዮጵያ ሕዝብ በጣም ጠቃሚ ይሆናል ብለን እናምናለን፡፡
ተርጓሚው በዚህ ትርጉም ላይ መስራት የጀመረው ከጥር 2004/2012 ዓም ጀምሮ ነው፡፡ በ2007/2015 የዮሐንስ ወንጌል ትርጉም ተጠናቆና ታትሞ ለወንጌል ሥርጭት አገልግሎት እንዲውል በነፃና ብዛት ተሰራጭቷል፡፡ አሁን ደግሞ የሙሉው አዲስ ኪዳንና የመጽሐፈ መዝሙር ትርጉም ተጠናቆ፣ ታርሞና ተስተካክሎ በመጠናቀቁ በያዝነው ዓመት ማለትም 2013/2021 እንደሚታተምና እንደሚሰራጭ ይጠበቃል፡፡ ከዚያም
የሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ቀጥሎ በ2025 እንደሚጠናቀቅና ለአንባቢዎችና ለእግዚአብሔር አገለግሎት እንደሚሰራጭ ከብርቱ ፀሎት ጋር ተስፋ ይደረጋል፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ይህን ቀጥተኛውን የአዲስ ኪዳንና የመጽሐፈ መዝሙር ትርጉም ለማሳተም የሚያስፈልገውን የገንዘብ ምንጭ እየፈለግን ነው፡፡ ይህን ክቡር ቃል ማሳተምና ወደ ኢትዮጵያ ማጓጓዝ ሂደት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን
ቃል ለሕዝቡ ማዳረስ አስፈላጊ ስለሆነ እግዚአብሔር እንደሚረዳን ፅኑ እምነታችንና ፀሎታችን ነው፡፡
ቪዲዮዎች
VIDEO
የመስመር ላይ ቅዱሳን ጽሑፎች እና ጽሑፎች
መጽሐፍ ቅዱስ
አማርኛ Words of Life የቀን መቁጠሪያዎች
ለ 2019 በቀለማት ያሸበረቀ የቀን መቁጠሪያ በአማርኛ እና በአካባቢያችን ከሚገኙ ሃገሮች ውስጥ በአብዛኛው በእንግሊዝኛ እና በአስደናቂ ሁኔታ የያዛቸውን ፎቶግራፎች ያቀርባል.የግብዓት የቀን መቁጠሪያዎች ከ TBS መደብር ይግዙ.
የየዓመቱ ጥቅል ሪፖርቶች
ዝርዝሮችን ለማየት አንድ ዓመት ይምረጡ
2018 / 2010 ዓም
የአማርኛው ተርጓሚ የአዲስ ኪዳንን ትርጉም የመጀመሪያ ደረጃ በዚህ ዓመት አጠናቋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ትርጉም በተጠናቀቀ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ተርጓሚው ባለቤቱና ልጆቹ መጥፎ የመኪና አደጋ አጋጥሟቸው ነበር፡፡ የቤተሰቡ አባላት ከፍተኛ ጉዳት ባይደርስባቸውም፣ ተርጓሚውና ባለቤቱ በደረሰባቸው ጉዳት ሆስፒታል ውስጥ የሚያስቆይ ሕክምናና ተመላላሽ ክትትል ተደርጎላቸዋል፡፡ አሁን ሁለቱም ተሽሏቸው በደህና
ሁኔታ ላይ በመሆናቸው ጌታን እናመሰግናለን፡፡ ትርጓሚውም የአዲስ ኪዳንን የመጀመሪያ ትርጉም ወደማረምና ማስተካከል ስራው ተመልሷል፡፡ በዚህም ስራ ትርጉሙን ከግሪኩ ጋር እያስተያየ አስፈላጊ ማስተካከያዎችንና የለቀማ እርማቶችን እያደረገ ነው፡፡ ይህንን ደረጃ ለማጠናቀቅ ታማኝ የሆኑና እራሳቸውን ለዚህ ስራ የሚሰጡ የጥራት እርምት አንባቢዎች ለስራው መጠናቀቅ በጣም ያስፈልጋሉ፡፡
2017 / 2009 ዓም
የአማርኛው ትርጉም አዘጋጅ አዲስ ኪዳንን ከግሪክ ወደ አማርኛ በመተርጎም ስራው በጣም ጥሩ ስራዎችን እያጠናቀቀ ነው፡፡ ከማቴዎስ ወንጌል እስከ ሁለተኛ ተሰሎንቄ፣ የአንደኛ ዮሐንስን ጨምሮ በመጀመሪያ የትርጉም ደረጃ ተጠናቀዋል፡፡ የዮሐንስ ወንጌል በ2007 ዓም ታትሞ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፡፡ የሉቃስ ወንጌል በመጀመሪያ ደረጃ ትርጉምና የመጀመሪያ ደረጃ እርምት ንባብ ተጠናቋል ፡፡ ተርጓሚያችን
አሁን ባለበት በአሜሪካ ውስጥ ተገቢ የሆኑ የጥራተ እርምት ንባብ አጋዦችና ተባባሪዎች እየተገኙ ነው፡፡ ተርጓሚውም የአዲሱን የአማርኛ ትርጉምን ስራ አስፈላጊነት የሚገልፅ መጽሐፍን እያዘጋጀ ሲሆን፣ ይህንኑ የሚያስረዳ የፖወር ፖይንት ዝግጅቶችን አጠናቆ በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ እያቀረበ ይገኛል፡፡
2016 / 2008 ዓም
የስላሴያውያን መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር Trinitarian Bible Society ለማጓጓዣ የሚያስፈልጉ ተጨማሪ ወጪዎችን ካደረገ በኋላ 100 000 የሚጠጉ የአማርኛ የዮሐንስ ወንጌሎች ኢትዮጵያ ደርሰዋል፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራትም በኢትዮጵያ ውስጥ በነፃ ተሰራጭተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የሉቃስ ወንጌል ትርጉምና የመጀመሪያ የጥራት ንባብ ተካሂዷል፡፡ የማቴዎስ ወንጌል፣ የማርቆስ ወንጌልና የአንደኛ ዮሐንስ
ለእርምት ንባብ ዝግጁዎች ሆነዋል፡፡ የሐዋርያት ስራም በከፊል ተተርጉሟል፡፡
2015 / 2007 ዓም
ባለፈው ዓመት ውስጥ የአማርኛ ተርጓሚያችን በጣም ጥሩ የሆነ እድገት አድርጓል፣ የዮሐንስ ወንጌል ትርጉምና ንባበ ጥራት ስራ ተጠናቋል በመቀጠልም የሉቃስ ወንጌልና የማቴዎስ ወንጌሎች እንዲሁም የማርቆስ ከፊል ትርጉሞች ተጠናቀዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ 100 000 የአማርኛ የዮሐንስ ወንጌል ታትሞ አሜሪካ ውስጥ በMilford, Ohio በሚገኘው በBearing Precious Seed አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ
ለመጓጓዝ በዝግጅት ላይ ነው፡፡ ወንጌሎቹ በኢትዮጵያ ውስጥ በነፃ እንዲሰራጩም ድጋፍ የሚያደርገው firstBible International ነው፡፡
2014 / 2006 ዓም
የዮሐንስ ወንጌል ሦስተኛ ዙር እርማት እና መደበኛ የእርምት ንባበ ጥራት ስራ አልቋል፡፡ ይህ ትርጉም በድርጅቱ የትርጉም ጥራት ደረጃ መርሆ መሰረት ተፈትሾ እንዲታተም ተረጋገጧል፡፡ ይህ ለሕትመት ዝግጁ የሆነው የዮሐንስ ወንጌል በአሁኑ ጊዜ ታይፕሴት እየተደረገና ለመጨረሻ እርምት እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡
2013 / 2005 ዓም
እግዚአብሔር ቢፈቅድ የአዲሱ የአማርኛ የዮሐንስ ወንጌል ትርጉም በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ በመጽሐፍ መልክ ተተይቦ ይዘጋጃል፡፡ በዚህ ትርጉም ስራ ላይ እየሰራ ያለውን ተርጓሚ በእርምት ንባበ ጥራት የሚያግዙ ወገኖችን ጌታ እንዲሰጠው የፀሎት ጥያቄዎችን እናቀርባለን፡፡
2012 / 2004 ዓም
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ አዲስ ትርጉም ስራ ተጀምሯል፡፡ ይህ ትርጉም ከግሪኩና ከሒብሩው የመጀመሪያዎቹ ቅዱሳት መጽሐፍት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ሆኖም የመጀመሪያውንና በ1879 ወደ አማርኛ የተተረጎመውን የአባ አብርሃምን ትርጉም ያገናዘበ ነው፡፡ ይህንን ትርጉም የሚያከናውነውና የሚመራው ለዚህ ስራ ትልቅ ሸክም ያለው አንድ ኢትዮጵያዊ ፓስተር ነው፡፡